ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2012 የውድድር ዘመንን በ24 ቡድኖች ማዋቀሩን ተከትሎ እኛን ማካተት ይገባዋል ሲል ደሴ ከተማ ለፌዴሬሽኑ በደብዳቤ አቤቱታውን አቀረበ።
ደሴ በደብዳቤው በከፍተኛ ሊግ በሦስቱም ምድቦች ከአንድ እስከ አራት የወጡ ቡድኖችን በማካተት የተወዳዳሪ ክለቦች ቁጥር ወደ በ28 ከፍ እንዲል እና ደሴ ከተማ በዚህ ውድድር ውስጥ እንዲገባ የሚል ጥያቄ መስከረም 7 ቀን 2012 ለፌዴሬሽኑ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።
ደሴ ከተማ ይህ የፎርማት የተወሰኑ ክልል ቡድኖችን ብቻ የሚጠቅም መሆኑንን ገልጾ እግርኳስ ፌዴሬሽኑ በ2011 ውድድር ዓመት መጀመሪያ ላይ የተሰጠው መመርያ በየምድቡ አንደኛ የሆነ ወደ ፕሪምየር ሊግ ያድጋል የሚል የነበረ በመሆኑ በዚህ ምክንያት ቡድናችን በሂሳብ ስሌት ከአንደኝነት ሲርቅ ለወጣቶቹ እድል በመስጠት የውድድር መርሀ ግብሩን ለመጨረስ ያህል አከናውኗል። በዚህም ምክንያት ማግኘት የነበረብንን ነጥብ አጥተናል። ይህ ታሳቢ ተደርጎም ፎርማቱ በድጋሚ መታየት አለበት ሲል ጠይቋል።
© ሶከር ኢትዮጵያ