ሰበር ዜና | የፕሪምየር ሊጉ አዲሱ ፎርማት ውድቅ ሆነ

ፌዴሬሽኑ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2012 የውድድር ዘመን 24 ቡድኖች በሁለት ምድብ ከፍሎ እንዲደረግ የወሰነው ውሳኔ ውድቅ ሆነ።

የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን የዘጠኙ የክልልና የ2ቱ ከተማ መስተዳድር እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንቶች፣ የስፖርት ኮሚሽን አመራሮች እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አመራሮች በተገኙበት የውይይት መድረክ ከብዙ ውይይቶች በኋላ ነው ውሳኔው ውድቅ የሆነው።እንደ ምክንያት የቀረበውም ጥናት ያልተጠናበት እና የክለቦችን ይሁንታ ያላገኘ በመሆኑ እንዲሁም ህዝብን ከህዝብ የሚለያይ በመሆኑ እንደሆነ ሰምተናል።

በቀጣይ ሊጉ በምን መልኩ ይቀጥላል የሚለው ጉዳይ ክለቦቹ ተመካክረው እንዲወስኑ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ዝርዝር መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን


© ሶከር ኢትዮጵያ