ጀሚል ያዕቆብ ወደ ጅማ አባጅፋር አቅንቷል

ወልዋሎ ለመቀላቀል ተስማምቶ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ጀምሮ የነበረው ጀሚል ያዕቆብ ለጅማ አባጅፋር ፊርማውን አኑሯል።

ከወራት በፊት ኢትዮጵያ መድንን ለቆ ወልዋሎ በመቀላቀል ላለፈው አንድ ወር ከቡድኑ ጋር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ የቆየው የተከላካይ ክፍል ተጫዋቹ ጀሚል ከክለቡ ጋር የተለያየበት ምክንያት ባይታወቅም ቀጣይ ዓመት የጅማ አባጅፋር ማልያ ለብሶ እንደሚጫወት ተረጋግጧል።

ባለፈው ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ጥሩ ዓመት ያሳለፈው ተከላካዩ የጅማ አባጅፋር አምስተኛ ፈራሚ ሲሆን ከዚህ ቀደም ለሌላው የከተማው ክለብ ጅማ አባ ቡና መጫወቱ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ