የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ደብዳቤዎች ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ልኳል።
በመጀመርያ የተላከው ደብዳቤ ፌደሬሽኑ ጥቅምት አንድ ከሚያካሄደው የፌደሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ በፊት የጥናት ፅሁፍ ማቅረብ እንደሚፈልግ የገለፀለት ነው። ፌዴሬሽኑ በሊግ አደረጃጀት፣ አሰራር እና የአመራር ችግሮችን የሚዳስስ እና የሚያስቀምጥ ጥናት ማዘጋጀቱ ሲገልፅ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ለባለ ድርሻ አካላት ጥሪ እንዲያደርግለትም ጨምሮ ገልጿል።
ሁለተኛው ደብዳቤ ጥቅምት 1 የሚካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በአጀንዳነት የተያዘው ውስብስብ ችግሮች ያሉበት የረቂቅ ማሻሻያ መተዳደርያ ደንብ ለጉባዔው መቅረብ እንደሌለበት የገለፀበት ነው።
ዝርዝሩን ደብዳቤው ላይ ይመልከቱ፡-
© ሶከር ኢትዮጵያ