ሀዲያ ሆሳዕና የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈረመ

ሀዲያ ሆሳዕና የአማካይ ሥፍራ ተጫዋቹ በኃይሉ ተሻገረን አስፈረመ፡፡

ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ የተስፋ ቡድን ከተገኘ በኃላ በቀይ ለባሾቹ ዋናው ቡድን ላለፉት አምስት ዓመታት ቆይታ ያደረገው ይህ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ከዚህ ቀደምም ለኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን መጫወት ችሏል።

ከበኃይሉ ቀደም ብሎ እንደአብዱልሰመድ ዓሊ፣ አፈወርቅ ኃይሉ እና ይሁን እንደሻው የመሳሰሉ አማካዮችን ያስፈረመው ሀዲያ ሆሳዕና በአዲሱ የውድድር ዓመት ጠንካራ የአማካይ ክፍል ይዞ ብቅ እንደሚል ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ