ፌደሬሽኑ ከክለቦች ጋር ይወያያል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ቀጣይ ዓርብ በኢሊሌ ሆቴል ከክለቦች ጋር ውይይት ያደርጋል።

በዚ ወቅት የእግር ኳስ ማኅበረሰቡ መነጋገርያ የሆነው የፕሪምየር ሊጉ ፎርማትን ጨምሮ በርካታ ሃሳቦች ይነሱበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ውይይት ምን ያህል ክለቦች እንደሚሳተፉበት የታወቀ ነገር ባይኖርም በርካታ ነጥቦች እንደሚነሱበት ከወዲሁ ለማወቅ ተችሏል።

ባለፈው ሳምንት የፌደሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ አባላት በፌደሬሽኑ ፅህፈት ቤት ባደረጉት ስብሰባ ፌደሬሽኑ በሊጉ ፎርማት እና ውድድሩ በምን አግባብ እንዲካሄድ ከክለቦች ጋር የቅርብ ውይይት እንዲካሄድ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት የሚካሄደው ይህ ተጠባቂ መድረክ ከተጠቀሰው አጀንዳ ሌላ የሊግ ካምፓኒ ጉዳይም ጥልቅ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ የውይይት መድረክ እስካሁን ድረስ በኢሊሌ ሆቴል ይካሄዳል ቢባልም የቦታ ለውጥ ሊኖር እንደሚችልም ይገመታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ