አዳማ ከተማ የሁለት ተጫዋቾቻቸውን ውል አድሰዋል

ቀደም ብለው ወደ ዝውውር በመግባት የቀድሞ አሰልጣኛቸው አሸናፊ በቀለን በመቅጠር ተጫዋቾች ያስፈረሙት አዳማ ከተማዎች የሁለት አማካዮቻቸው ውል አድሰዋል።

ከሱዳኑ አልአህሊ ሸንዲ መልስ ላለፉት ሦስት ዓመታት ከአዳማ ከተማ ጋር ቆይታ ያደረገው የአማካይ ክፍል ተጫዋቹ አዲስ ህንፃ ከቻምፒዮኖቹ መቐለ 70 እንደርታዎች ጋር ስሙ በስፋት ሲነሳ ቆይቶ ከቡድኑ ልምምድ መስራት ቢጀምርም መጨረሻ ላይ ዝውውሩ ባለመሳካቱ ከአዳማ ከተማ ለመቀጠል ተስማምቷል።

ሌላው በአዳማ ከተማ ውሉን ያደሰው አይቮሪኮስታዊው ኢስማኤል ሳንጋሪ ነው። በ2010 ውድድር ዓመት ለአዳማ ከተማ መጫወት የጀመረው ይህ ተጫዋች ላለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት ጥሩ ብቃት አሳይቶ በደጋፊዎች ከፍተኛ ተወዳጅነት ማትረፉ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ