‘ ሰሜናዊት ኮከብ ‘ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ በቅርቡ ስራ ይጀምራል

በመቐለ ሴት ታዳጊዎችን ያካተተ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል በቅርቡ ሥራ ይጀምራል።

ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በህፃናት እና ታዳጊዎች ያተኮሩ የእግር ኳስ ማሰልጠኛዎች መከፈት መጀመራቸው ይታወሳል። አሁን በቅርቡ በመቐለ ይከፈታል የተባለው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ ደግሞ ብዙም ባልተለመደ መልኩ የሴት ህፃናት ሰልጣኞች ያካተተ መሆኑ ሲታወቅ በሃገራችን ከተለመደውን የእግር ኳስ ሥልጠና መጀመርያ ዕድሜ በመቀነስ ህፃናት በዘጠኝ ዓመት ዕድሜያቸው እግር ኳስ እንዲጀምሩ ለማድረግ እንደታሰበ ለማወቅ ተችሏል።

በሦስት የዕድሜ እርከኖች ከ9-12 ፣ 13-14 እና 15-17 ያካተተው ይህ ማሰልጠኛ ሴት ሰልጣኞች ከ13 ዓመታቸው ጀምሮ ስልጠና የሚወስዱበት ዕድልም ማመቻቸቱ ለማወቅ ተችሏል።

በአሰልጣኝ ጎይቶም አማረ እና አሰልጣኝ ሃብቶም ኃይሉ የሚመራው ይህ የማሰልጠኛ ተቋም እንዳ ፀባ የተባለ ሜዳን ጨምሮ በሁለት ሜዳዎች እንደሚደረግም አዘጋጆቹ ገልፀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ