2020 የቻን ማጣሪያ ላይ እየተካፈለ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመቐለ ስታዲየም በሩዋንዳ አቻው በመጀመሪያው ጨዋታ 1-0 ሽንፈት የገጠመው ሲሆን ለመልሱ ጨዋታ ዝግጅት ለማድረግ አሰልጣኝ አብረሃም መብራቱ እና ረዳቶቻቸው ለ24 ተጫዋቾች ጥሪን አድርገዋል ፡፡ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ በአዳማ ከተማ ኤክስኪውቲቭ ሆቴል ማረፊያቸውን በማድረግም ዝግጅት የሚጀምሩ ይሆናል፡፡
ግብ ጠባቂዎች(3)፡ ምንተስኖት አሎ (መከላከያ)፣ ጀማል ጣሰው ( ፋሲል ከነማ)፡ ለዓለም ብርሃኑ (ቅ/ጊዮርጊስ)
ተከላካዮች(8)፡ አስቻለው ታመነ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ደስታ ደሙ (ቅ/ጊዮርጊስ)፣ ያሬድ ባዬ (ፋሲል ከነማ)፣ አንተነህ ተስፋዬ (መከላከያ)፣ አህመድ ረሺድ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ጌቱ ኃ/ማሪያም (ሰበታ ከተማ)፣ መሳይ ጳውሎስ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ረመዳን የሱፍ (ስሁል ሽረ)
አማካዮች(6)፡ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ፍፁም ዓለሙ (ባህር ዳር ከተማ)፣ ሀይደር ሸረፋ (ቅ/ጊዮርጊስ)፤ ዮናስ በርታ(አዳማ ከተማ)፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ) ፡ ከነዓን ማርክነህ (አዳማ ከተማ)
አጥቂዎች(7) ፡ አስቻለው ግርማ (ሰበታ ከተማ)፣ ፉአድ ፈረጃ (አዳማ ከተማ)፣ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል (መቐለ 70 እንድርታ)፣ ሙጂብ ቃሲም (ፋሲል ከነማ)፣ ፍቃዱ ዓለሙ (መከላከያ)፣ አዲስ ግደይ (ሲዳማ ቡና)
© ሶከር ኢትዮጵያ