ጥቅምት 1 ቀን ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 11ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ወደ ሌላ ቀን ሊራዘም ነው።
መካሄድ ከነበረበት ጊዜ በአንድ ሳምንት ዘግይቶ ጥቅምት 1 ቀን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አስቀድሞ ይፋ ቢያደርግም ለጊዜው ምክንያቱ ባልተገለፀ ሁኔታ የሚደረግበት ቀናት ተገፍቶ ወደ ጥቅምት 29 ቀን (ከዚህም ቀን ሊያጥርም ሊረዝምም ይችላል) ለማደረግ እንደታሰበ ሰምተናል።
ለወትሮም ውዝግቦች የማያጡት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ የተለመደው
የ2010 ዕቅድ አፈፃፀም፣ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ መወያየት ማፅደቅ እና በተጓደሉ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ማሟላት እንዳለ ሆኖ ከወዲሁ ብዙ ክርክሮች ያስነሳል ተብለው የሚጠበቁ በርከት ያሉ አዳዲስ አጀንዳዎች በዕለቱ ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
© ሶከር ኢትዮጵያ