ፌዴሬሽኑ የመሻርያ ደብደቤ ለክለቦች ላከ

በ2012 የውድድር ዘመን ወደ ፕሪምየር ሊግ አድጋችኋል ለተባሉት የከፍተኛ ሊግ አምስት ቡድኖች እና ከፕሪምየር ሊጉ ለወረዱ ሦስት ቡድኖች የመሻርያ ደብዳቤ ልኳል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ከፀጥታ ስጋት ጋር በተያያዘ በ2012 የተሳታፊ ቡድኖችን ቁጥር ወደ 24 አሳድጎ በሁለት ምድብ ለማካሄድ ወስኖ ነበር። በዚህም መሠረት ከፕሪምየር ሊጉ ለወረዱት መከላከያ ፣ ደቡብ ፖሊስ እና ደደቢት እንዲሁም በከፍተኛ ሊግ ለሚገኙት ለገጣፎ ለገዳዲ ፣ አርባምንጭ ከተማ ፣ ኢትዮጵያ መድን ፣ ኢኮስኮ እና ነቀምቴ ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደጋቸውን ፌዴሬሽኑ በደብዳቤ ማሳወቁም ይታወቃል።

ሆኖም ሊከሰት የሚችለውን የፀጥታ ስጋት መንግስት ኃላፊነት እንደሚወስድ በመግለፁ ውድድሩ ለስፖርቱ እድገት በሚሆን መልኩ አስኪዱ ብሎ አቅጣጫ በመስጠቱ ፕሪምየር ሊጉ በነበረት እንዲቀጥል በመወሰኑ ክለቦቹ በዘንድሮ ዓመት በከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪ መሆናችሁን አውቃችሁ እንድትዘጋጁ ይህን የመሻርያ ደብዳቤ ተልኳል።

* የመጀመርያው እና የመሻርያው ደብደቤ እነዚህን ይመስላሉ



© ሶከር ኢትዮጵያ