መከላከያ ፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጠው ጠየቀ

ፌዴሬሽኑ የህግ አግባብን ተከትሎ ባለመወሰኑ ምክንያት የውሳኔው መቀያየር በክለባችን ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳደረ በመሆኑ አስቸኳይ ምላሽ ይሰጠን በማለት መከላከያ አቤቱታውን አቀረበ።

የመከላከያ አቤቱታ ዝርዝር በዋናነት ሦስት ነጥቦች ላይ ያተኩራል።

1ኛ ወልዋሎ ከሽረ ያድጉት ጨዋታ ላይ የወልዋሎ ተጫዋቾች ከነበረው የፀጥታ ስጋት አኳያ ተፅእኖ ውስጥ በመግባት ከአቅም በታች እንዲጫወቱ ተደርጓል። በዚህም ስሑል ሽሬ ከፍተኛ የዲሲፒሊን ጥሰት በመፈፀም ያለአግባብ ሦስት ነጥቦች ስለማግኘቱ ያቀረብነው አቤቱታ ምላሽ አላገኘም።

2ኛ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንደምንሳተፍ ፌዴሬሽኑ በላከው ደብዳቤ መሠረት ከፍተኛ በጀት በመመደብ የተጫዋቾች ዝውውር እና ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን የቅድመ ውድድር ዝግጅታችንን አዳማ ላይ እየሰራን ባለበት ወቅት ውሳኔውን መቀልበሱ የክለቡን አመራሮች ፣ ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች ሞራል ያልጠበቀ ነው።

3ኛ ውድድሩ በ16 ክለቦች ይቀጥላል ከተባለ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፎርፌ ከተነሳ ጨዋታው ያላለቀ በመሆኑ ወራጅም ሆነ ቻምፒዮን የሆነ ክለብ የለም ፤ የተሰጠው ውሳኔም አግባብነት የለውም የሚል እና ሌሎች ዘርዘር ያሉ ጉዳዮችን በአቤቱታ ደብዳቤ ውስጥ አካቷል።

* አጠቃላይ የደብዳቤው ይዘት ይሄን ይመስላል፡-


© ሶከር ኢትዮጵያ