የኢትዮጵያ ዋንጫ ዘንድሮም በፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊዎች መካከል ብቻ ይካሄዳል፡፡ ፌዴሬሽኑ ባወጣው እጣ መሰረትም የካቲት 6 ቀን 2008 የመጀመርያ ዙር ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
የእጣ ማውጣቱ የተከናወነው ክለቦቹ ባለፈው የውድድር ዘመን ባስመዘገቡት ውጤት መነሻነት ሲሆን የሊጉ ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ እና 2ኛ ደረጃን ያገኘው ደደቢት ጨዋታቸውን ከሩብ ፍፃሜው ጀምሮ ያደርጋሉ፡፡
የመጀመርያው ዙር ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
ሀሙስ የካቲት 3 ቀን 2006
09:00 ሀዋሳ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ (አአ)
10:00 ኤሌክትሪክ ከ አዳማ ከተማ (አበበ ቢቂላ)
11:30 ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዲያ ሆሳዕና (አአ)
አርብ የካቲት 4 ቀን 2006
08:00 ሲዳማቡና ከ ዳሽን ቢራ (አበበ ቢቂላ)
10:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢት. ንግድ ባንክ (አበበ ቢቂላ)
* የመከላከያ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ ወደፊት እንደሚገለፅ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡
ያጋሩ