ወልዋሎ 2010 ጥር ወር ላይ አሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚአብሔር ውል እያላቸው በማሰናበቱ ምክንያት ቀሪ ደሞዛቸውን እንዲከፍል የተወሰነበት ውሳኔን ተፈፃሚ ባለማድረጉ የእግድ ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 2009 ላይ ወደ ፕሪምየር ሊጉ በአሰልጣኝ ብርሀኔ ገብረእግዚአብሔር ካደገ በኃላ በሊጉ እየተሳተፈ የሚገኘው ወልዋሎ 2010 ላይ በአሰልጣኙ እየተመራ ሊጉን ቢጀምርም ከውጤት መጥፋት ጋር በተያያዘ በዛኑ ዓመት ጥር ወር ላይ ለማሰናበት ተገዷል፡፡
ይሁንና በወቅቱ አሰልጣኙ ሲሰናበቱ በስምምነት እንደተለያዩ ተገልፆ የነበረ ቢሆንም አሰልጣኝ ብርሀኔ የስድስት ወር ኮንትራት አለኝ በማለት ለፌዴሬሽኑ የክስ ደብዳቤን አስገብተው ፌዴሬሽኑም ክለቡ ለአሰልጣኙ በውላቸው መሠረት ክፍያን እንዲፈፅምላቸው መወሰኑ ይታወቃል። ሆኖም ክለቡ ይህን ተፈፃሚ ሊያደርግ ባለመቻሉ ክፍያውን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ከፌዴሬሽኑ ምንም ዓይነት አገልግሎት እንደማያገኝ ለክለቡ አሳውቋል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ