ሴቶች ዝውውር | ሀዋሳ ከተማ ዘጠኝ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነባሮችን ውልም አድሷል

የዐምናው የሴቶች ጥሎ ማለፍ አሸናፊ ሀዋሳ ከተማ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአስር ነባሮችን ውል አድሷል። ከወጣት ቡድኑ ደግሞ ሦስት ተጫዋቾችን አሳድጓል፡፡

የቀድሞዋ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ዓይናለም አሳምነው በድጋሚ ከንግድ ባንክ ወደ ክለቡ ስትቀላቀል የጥረት ኮርፖሬቷ አጥቂ ምስር ኢብራሂምም ለሀዋሳ ከፈረሙ ተጫዋቾች አንዷ ሆናለች። ይታገሱ ተገኝወርቅ (አጥቂ/አዳማ ከተማ)፣ ትውፊት ካዲዮ (አጥቂ/ድሬዳዋ ከተማ)፣ ጫልቱ ተኬሳ (አጥቂ/አቃቂ ቃሊቲ)፣ ዙፋን ደፈርሻ (አማካይ/አቃቂ ቃሊቲ)፣ ገነት ገብረማርያም (ተከላካይ/አርባምንጭ)፣ ገሊላ አበራ (ግብ ጠባቂ/ሻሸመኔ ከተማ)፣ ቤተልሄም ዮሀንስ (ግብ ጠባቂ/ጌዲኦ ዲላ) ሌሎች ሀዋሳን የተቀላቀሉ አዲስ ተጫዋቾች ናቸው።

የክለቡ ቁልፍ ተጫዋቾች የነበሩት ግብ ጠባቂዎቹ ዓባይነሽ ኤርቄሎ እና ገነት ኤርሚያስ፣ ተከላካዮቹ ትዝታ ኃይለሚካኤል፣ ዓይናለም አደራ እና ካሰች ፍሰሀ፣ አማካዮቹ መቅደስ ማሞ፣ ቅድስት ቴካ አማካይ እና ሳራ ኬዲ፣ አጥቂዎቹ መሳይ ተመስገን እና ነፃነት መና ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ስምምነት ፈፅመዋል፡፡

በተያያዘ በዓመቱ ታዳጊዎችን ከB ቡድኑ የሚያሳድገው ሀዋሳ ከተማ ዘንድሮም ታሪኬ ጴጥሮስ፣ ቃልኪዳን ወንድሙ እና ማሳንቱ ኤቢሶ የተባሉ ተጫዋቾችን አሳድጓል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ