የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ይካሄድ ይሆን ?
Share
የ2011 የውድድር ዘመን የፕሪምየር ሊጉ ቻምፒዮን መቐለ 70 እንደርታ እና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው ፋሲል ከነማ መካከል የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ መቼ ይካሄድ ይሆን?
የፕሪምየር ሊጉ ዐቢይ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው የመጀመርያው ስብሰባ በዚህ ጨዋታ ዙርያ ምንም እንዳልተነጋገረ አረጋግጠናል። ይህ ውድድር አዲሱን የፕሪምየር ሊግ ኮሚቴን የማይመለከት እና በቀድሞ የሊግ ኮሚቴ የሚመራ በመሆኑ ጉዳዩን ሳይመለከቱት እንደቀሩ ሰምተናል።
ፌዴሬሽኑ በዚህ ውድድር ዙርያ ያሰበው ነገር ካለ ብለን ለማጣራት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን የውድድሩ መካሄድ አለመካሄዱን አስመልክቶ በቀጣይ መረጃዎችን ካገኘን የምንመለስበት ይሆናል።
በፌዴሬሽኑ ትኩረት ማጣት በተለያዩ ጊዜያት አንዴ እየተካሄደ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሳይካሄድ እየቀረ ሲቆራረጥ የቆየው የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ዘንድሮም የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ አድርጎታል።
© ሶከር ኢትዮጵያ
ተዛማጅ ፅሁፎች
የአሰልጣኞች አስተያየት | አዲስ አበባ ከተማ 1-1 ጅማ አባ ጅፋር
የረፋዱ የ25ኛ ሳምንት የመጀመርያ ጨዋታ በአንድ አቻ ከተጠናቀቀ በኋላ አሰልጣኞች አስተያየት ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው - አዲስ አበባ ስለጨዋታው “የምንስታቸው...
ሪፖርት | አዲስ አበባ አሁንም መሪነቱን ማስጠበቅ ሳይችል ቀርቷል
በ25ኛ የጨዋታ ሳምንት የመክፈቻ በነበረው መርሐግብር አዲስ አበባ ከተማ ለአምስተኛ ተከታታይ ጨዋታ አስቀድሞ መምራት ቢችልም በመጨረሻ ባስተናገደው ግብ ከጅማ አባ...
ቅድመ ዳሰሳ | የ25ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎች
ሊጉ ለብሔራዊ ቡድን ዝግጅት እና ጨዋታዎች ከመቋረጡ በፊት የሚደረጉት የጨዋታ ሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ፍልሚያዎች እንዲህ ተዳሰዋል። አዲስ አበባ ከተማ ከ...
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ | 24ኛ ሳምንት ምርጥ 11
እንደ ሁልጊዜው ባሳለፍነው ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ላይ ጎልተው የወጡ ተጫዋቾችን ያካተተ ቡድን ሰርተናል። አሰላለፍ (4-3-2-1) ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራ -...
ብሔራዊ ቡድኑ ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርቧል
የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ከቀናት በኋላ ማድረግ የሚጀምረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾቹ ጥሪ አስተላልፏል። በ2023 በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ...
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል
10:00 ላይ ከናይጄሪያ አቻው ጋር ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል። በሕንድ ለሚደረገው የሴቶች...