ደቡብ ፖሊስ ካስፈረማቸው በርካታ ተጫዋቾች ጋር እየተለያየ ነው

በፕሪምየር ሊጉ ተሳታፊ እንደሆነ በፌዴሬሽኑ በመገለፁ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነበረው ደቡብ ፖሊስ ውሳኔው ተሽሮ በከፍተኛ ሊጉ እንዲወዳደር በመወሰኑ ከአዲስ ፈራሚዎቹ ጋር እየተለያየ ነው፡፡

ክለቡ በውሳኔ ለውጡ መነሻነት ተጫዋቾቹን ለመልቀቅ የተገደደ ሲሆን በቀጣይም በርካታ ተጫዋቾችን እንደሚለቅ ተሰምቷል። በዚህም መሠረት ከአርባምንጭ ከተማ ክለቡን ተቀላቅለው የነበሩት አማካዩቹ ቴዲ ታደሰ እና አስጨናቂ ፀጋዬ፣ ከወላይታ ድቻ ፈርመው የነበሩት ተክሉ ታፈሰ እና ሀብታለም ታፈሰ ከክለቡ ሲለያዩ ከወላይታ ድቻ ቢጫ ለባሾቹን ተቀላቅሎ የነበረው ሀይማኖት ወርቁን ሊለያይ ከሚችሉት መካከል መሆኑን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ክለቡ አሁንም ድረስ በፌድሬሽኑ ላይ ቅሬታውን እያቀረበ ሲሆን በቀጣይም ምላሽ ማግኘት የማይችል ከሆነ ከተጨማሪ ተጫዋቾች ጋር የመለያየቱ ጉዳይ ዕርግጥ ይሆናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ