ሰበታ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ ሲሾም የግብ ጠባቂ አሰልጣኙን ውል አራዝሟል

ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በፋሲል ከነማ ሲሰራ የነበረው ይታገሱ እንዳለ የሰበታ ከተማ ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ ሲሾም የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ አዳሙ ኑሞሮ ውልም ተራዝሞለታል፡፡

የቀድሞው የአዳማ ከተማ ተጫዋች ይታገሱ በአዳማ ከተማ የታዳጊ ቡድኖችን በማሰልጠን የአሰልጣኝነት ህይወትን የጀመረ ሲሆን በ2011 ደግሞ ውበቱ አባተ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ በመሆን ሲሾሙ አሰልጣኙ በረዳትነት አብረው መስራት ችለዋል።

በክለቡ ባለፉት ሁለት ዓመታት የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ በመሆን ሲሰራ የነበረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ አዳሙ ኑሞሮ ለተጨማሪ ዓመት በሰበታ ከተማ ቆይታ ለማድረግ ውሉን አራዝሟል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ