የ2020 ቻን ተሳታፊዎች ተለይተው ታውቀዋል

በቀጣይ ዓመት በካሜሩን የሚዘጋጀው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ተሳታፊዎች ዛሬ ሙሉ ለሙሉ ሲታወቁ በርካታ ትላላቅ ሃገራት ወደ ውድድሩ አያመሩም።

በውድድሩ በአህጉሪቱ ላይ ጥሩ ስም ያላቸው ጋና፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካ እና ግብፅ የመሳሰሉ ሀገራት የማይካፈሉ ሲሆን በተቃራኒው በርካታ ያልተገመቱ ቡድኖችን ያሳትፋል። አዘጋጇ ካሜሩን፣ ታንዛንያ፣ ሩዋንዳ፣ ዩጋንዳ፣ ዛምቢያ፣ ናሚቢያ፣ ቶጎ፣ ሞሮኮ፣ ዚምባብዌ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ቱኒዝያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ጊኒ፣ ኒጀር እና ማሊ ይሳተፉበታል።

በሃገር ውስጥ ሊጎች ለሚጫወቱ ተጫዋቾች ዕድል ለመስጠት በሚል በ2009 የተጀመረው ይህ ውድድር ከዚ በፊት አምስት ግዜ መካሄዱ ሲታወስ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሁለት ግዜ ዋንጫ በማንሳት ትመራለች።

ቀጣይ ዓመት ጥር ወር ላይ በካሜሩን የሚካሄደው ይህ ውድድር ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት እንዲካሄድ ታስቦ ኢትዮጵያ በቂ ዝግጅት ባለማድረጓ የአዘጋጅነት ኃላፊነቱ ለካሜሩን መሰጠቱ ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ