በአሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ እየተመራ ባለፈው ዓመት ለመጀመርያ ጊዜ በተሳተፈበት የከፍተኛ ሊግ ውድድር በመጨረሻው ሳምንት በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው አቃቂ ቃሊቲ አስራ አንድ ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል።
ግብ ጠባቂው ሄኖክ አስጨናቂ (ዱከም ከተማ)፣ ሚኪያስ ደጄ (ለገጣፎ)፣ በተከላካይ ስፍራ ላይ የሚጫወቱት ባህሩ ከድር (ከፋ ቡና)፣ ሚኪያስ አዳሩ (ወሊሶ ከተማ) እና ትንሳኤ ደምሱ (ቦሌ ክፍለ ከተማ)፣ አማካዮቹ እስራኤል አበራ (08 ማዞሪያ)፣ አንዱዓለም ውጅራ (ናኖ ሁርቡ)፣ የአጥቂ ስፍራ ተሰላፊዎቹ አሰግድ ተድላ (08 ማዞሪያ)፣ እስማኤል አዳም (ሲልቫ ውሃ)፣ እንዳለ ፀጋዬ (ላስታ ላሊበላ) እንዲሁም በ2011 የውድድር ዓመት በኮከብ ግብ አግቢነት ሲፎካከር የነበረው ሚኪያስ አበራ (ገላን ከተማ) ለክለቡ የፈረሙ አዳዲስ ተጫዋቾች ናቸው።
በተያያዘ ዜና ቡድኑ የዋና አሰልጣኙ ፀጋዬ ወንድሙን ውል አራዝሟል። ከ2008 ጀምሮ ከቡድኑ ጋር የቆዩት አሰልጣኙ ቡድኑን እየመሩ ወደ ከፍተኛ ሊግ ማሳደግ የቻሉ አሰልጣኝ ናቸው።
© ሶከር ኢትዮጵያ