ለተጫዋቾች ለወራት ደሞዝ አለመክፈሉን ተከትሎ በፌዴሬሽኑ እግድ ተጥሎበት የቆየው ጅማ አባጅፋር እግዱ በገደብ መነሳቱ ቅሬታ አስነስቷል።
ፌዴሬሽኑ ጅማ አባጅፋሮች በቀጣይ የውድድር ዓመት በቃል የተስሟሟቸው ተጫዋቾች የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ አስድሞ ማፀደቅ እና ማስመዝገብ ስላለባቸው ቡድኑ እነዚህን ጉዳዮች እስኪያጠናቅቅ ድረስ እግዱ ዛሬ መነሳቱ ይታወቃል።
ይህን ተከትሎ ቅሬታ አቅራቢዎች ደሞዛችን አለመከፈሉ እየታወቀ እግዱ መነሳቱ ችግር ውስጥ ለምንገኘው ተጫዋቾች መፍትሔ እንዳናገኝ የሚያደርግ በመሆኑ ፌዴሬሽኑ ያልተከፈለን ደሞዝ ይከፈለን ሲሉ አቤቱታቸውን በደብዳቤ አሳውቀዋል።
የደብዳቤው ሙሉ ሀሳብ
© ሶከር ኢትዮጵያ