ከፍተኛ ሊግ | ደሴ ከተማ አስራ አራት አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል

በአሰልጣኝ አረጋይ ወንድሙ እየተመራ ባለፈው ዓመት በተሳተፈበት የከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ሦስት ጨዋታ እስከሚቀረው ድረስ ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማደግ ሲፎካከር የነበረው ደሴ ከተማ ለዘንድሮው የውድድር ዘመን በርካታ ተጫዋቾት በማስፈረም እያጠናከረ ይገኛል። እስካሁንም 14 ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

በግብ ጠባቂ ሥፍራ ላይ ባለፈው ዓመት ወልዲያ የተጫወተው ከፍያለው ኃይሉ እና በልእስቲ ቅረብ ከከፍተኛ ሊጉ ከወረደው አውስኮድ ፈርመዋል።

በተከላካይ ሥፍራ ላይ ምናሉ ተፈራ ከነገሌ ቦረና፣ ማታይ ሉል ከኢትዮጵያ መድን፣ የቀኝ መስመር ተሰላፊው ፍሬው ዓለማየሁ ከጋሞ ጨንቻ እንዲሁም የግራ መስመር ተጫዋቾቹ አብርሃም አሰፋ ከዳሞት እና ሄኖክ ብርሃኑን ከስሁል ሽረ አስፈርመዋል።

በአማካይ ስፍራ ላይ ተስሎች ሳይመን እና ሲሳይ ሚዲቂሳ ከወልዲያ ለደሴ ሲፈርሙ በድሉ መርዕድ ከአክሱም ከተማ ቡድኑን ተቀላቅለዋል።

በአጥቂ ስፍራ ላይ ተመስገን ዘውዱ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ቢንያም ተሻለ ከሰሎዳ ዓድዋ፣ ተካልኝ መስፍን ከሀዲያ ሆሳዕና እንዲሁም ሳምሶን ታሪኩ ከጎፋ ባሬንቺ ወደ ቡድኑ የመጡ ተጫዋቾች ናቸው።

ቡድኑ ከነባሮቹ መካከል የ11 ተጫዋቾችን ውል በማደስ በአጠቃላይ 25 ተጫዋቾችን ይዞ ከደሴ ከተማ ወጣ ብሎ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በማድረግ ላይ ይገኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ