በቅርቡ ከደመወዝ ክፍያ ጋር ቅሬታ ያነሱ የቀድሞ የወልቂጤ ከተማ ተጫዋቾች ለፌዴሬሽኑ ደብዳቤን ያስገቡ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ክለቡ ምላሽ እንዲሰጥ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡
በ2011 በወልቂጤ ከተማ ሲጫወቱ የነበሩ ስድስት ተጫዋቾች የሁለት ወር እና ከዚህ በላይ የደመወዝ ክፍያ አልተከፈለንም በሚል ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን አቤቱታን ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡ ፌዴሬሽኑም ጉዳዩን ተመልክቶ ክለቡ በአስር ቀናት ውስጥ ለፌዴሬሽኑ ምላሽን እንዲሰጥ ያዘዘ ሲሆን በሰባት ቀናትም ውስጥ የተጫዋቾቹን ቅሬታም እንዲፈታ በጊዜ ገደብ አማራጭ ለክለቡ ተሰጥቶታል። ይህን ማድረግ ካልቻለም በክለቡ ላይ እርምጃን እንደሚወስድ ለክለቡ በላከው ደብዳቤ ጠቁሟል፡፡
የደብዳቤው ሙሉ ይዘት
© ሶከር ኢትዮጵያ