በትላንትናው ዕለት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝነት ለመረከብ የተስማሙት እና በዛሬው ዕለት ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት የሚቆይ ውል የፈረሙት አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ለሴካፋ ውድድር የ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡
ከአራት ክለቦች ብቻ የተውጣጣው የተጫዋቾች ስብስቡ ላይ ገነት ኃይሉ፣ ትዝታ ኃይለሚካኤል እና መሳይ ተመስገንን የመሳሰሉ አዳዲስ ፊቶች ሲካተቱ ጥሩአንቺ መንገሻ ከረጅም ጊዜ በኋላ ጥሪ ደርሷታል።
በመጪው ህዳር 8 በታንዛኒያ አስተናጋጅነት በሚሰናዳው የሴካፋ የሴቶች ዋንጫ ላይ ኢትዮጵያ በምድብ ለ ከዩጋንዳ ፣ ኬንያና ጅቡቲ ጋር መደልደሏ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከመጪው ጥቅምት 23 ጀምሮ ልምምዳቸውን በአዲስ አበባ የሚጀምሩ ይሆናል፡፡
የተመረጡ ተጨዋቾች ስም ዝርዝር
ግብ ጠባቂዎች፡ ዓባይነሽ ኤርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ)፣ እምወድሽ ይርጋሸዋ (አዳማ ከተማ)፣ ታሪኳ በርገና (መከላከያ)
ተከላካዮች፡ ትዝታ ኃይለሚካኤል (ሀዋሳ ከተማ)፣ ገነሜ ወርቁ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ታሪኳ ደቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ዓለምነሽ ገረመው (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ጥሩአንቺ መንገሻ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ናርዶስ ዘለቀ (አዳማ ከተማ)፣ እፀገነት ብዙነህ (አዳማ ከተማ)፣ መስከረም ካንኮ (አዳማ ከተማ)፣ መሠሉ አበራ (መከላከያ)
አማካዮች፡ ሕይወት ደንጊሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ እመቤት አዲሱ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ብርቱካን ገብረክርስቶስ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ሰናይት ቦጋለ (አዳማ ከተማ)፣ ገነት ኃይሉ (አዳማ ከተማ)፣ አረጋሽ ከልሳ (መከላከያ)
አጥቂዎች፡ ሽታዬ ሲሳይ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ መሳይ ተመስገን (ሀዋሳ ከተማ)፣ ረሂማ ዘርጋው (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ሴናፍ ዋቁማ (አዳማ ከተማ)፣ ምርቃት ፈለቀ (አዳማ ከተማ)
© ሶከር ኢትዮጵያ