የአሰልጣኞች አስተያየት | ፋሲል ከነማ 2-0 ድሬዳዋ ከተማ

Read Time:29 Second

በአዳማ ከተማ ዋንጫ የዛሬ ሁለተኛ ጨዋታ ፋሲል በኦሰይ ማውሊ እና ሙጂብ ቃሲም ግቦች ታግዞ ድሬዳዋን 2-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ከጨዋታው በኋላም የፋሲል አሰልጣኝ አስተያየታቸውን ሲሰጡ የድሬዳዋውን አሰልጣኝ ስምኦን ዓባይ አስተያየት ማግኘት አልተቻለም።

“በዛሬው የቡድኔ እንቅስቃሴ ደስተኛ ነኝ።” ሥዩም ከበደ

ስለጨዋታው

“ቡድኑ ከወዳጅነት ወዳጅነት ጨዋታ እዚህ ላይ ደርሷል። በዛሬው የቡድኔ እንቅስቃሴ ደስተኛ ነኝ። በተለይም ተጋጣሚያችን ኳስ እንድንጫወት የሚፈቅድ መሆኑ እኛን ጠቅሞናል። ቡድኑ ጥሩ ነው ፤ አሁን ትንሽ ክፍተቶች ብቻ ነው የሚቀረን ይህንንም በቶሎ እናስተካክላለን።”

ስለአጥቂዎቹ ኳስ ማባከን

“ይህ ትልቅ ችግር ነው። በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ ያገኘነውን ንፁህ የሚባሉ የግብ ዕድሎች አባክነናል። እንዲህ ዓይነት ነገር ዋጋ ያስከፍላል ፤ በቀጣይ የሚሻሻል ይሆናል።”


© ሶከር ኢትዮጵያ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
ያጋሩ
error: Content is protected !!