ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰርቢያዊ ምክትል አሰልጣኝ ቀጠረ

ከወራት በፊት ሰርቢያዊ ዋና አሰልጣኝ የሾመው ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን ደግሞ ከአሰልጣኙ ጋር ከዚህ ቀደም በሀገራቸው አብረው መስራት የቻሉት ጉራን ጉዚያንን ረዳት እና የአካል ብቃት አሰልጣኝ በማድረግ መሾሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ጎራን ጉዚያን ፈረሰኞቹን በሁለት ዓመት የተቀላቀሉ ሲሆን በሰርቢያ፣ ግሪክ እና ቬትናም እና ጣሊያን ሀገራት ባሉ ክለቦች እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚገኙ ቡድኖች ውስጥ በአሰልጣኝነት እና በአካል ብቃት አሰልጣኝነት መስራት መቻላቸው ሲገለፅ በግሪክ ውስጥ በሚገኙ አራት የወንድ እና ሴት የእጅ ኳስ ቡድኖችን እንዲሁም ኦሊምፒያኮስ ውሀ ዋና ቡድን ከእግር ኳሱ ባለፈ አሰልጥነዋል፡፡ በአካል ብቃት ስልጠና የፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዳላቸውም ክለቡ ገልጿል።

ያለፉትን በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያዊያን ረዳት አሰልጣኞች እየተመራ የቆየው ክለቡ አሁንም እኚህ አሰልጣኝ ይምጡ እንጂ ዘሪሁን ሸንገታ በሦስተኛ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ሲቀጥሉ የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ኤሚ ንዲዚዬም በቦታቸው የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ