ከፍተኛ ሊግ | ጋሞ ጨንቻ አዲስ አሰልጣኝ ሲሾም አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

አዲስ አዳጊው ጋሞ ጨንቻ የቀድሞው አሰልጣኙ ማቲዮስ ለማን በዋና አሰልጣኝነት ሲቀጥር ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል።

ክለቡን ከዚህ ቀደም በአሰልጣኝነት መርተው የነበሩት እና ከ2010 ጀምሮ በአርባምንጭ ከተማ ረዳት አሰልጣኝነት ሲያገለግሉ የነበረው ማቲዮስ ለማን በድጋሚ የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የሾመ ሲሆን ነባር የቡድኑ አስራስምንት ተጫዋቾችንም ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል፡፡

አቤጋ ዓለሙ (ግብ ጠባቂ ከኮንሶ ኒውዮርክ)፣ ዳንኤል ዳና (አጥቂ ከቁጫ ፕሮጀክት)፣ የትምጌታ ታደሰ (አማካይ ከኮንሶ ኒውዮርክ)፣ ጌትነት ታደሰ (አማካይ ከፌደራል ፖሊስ)፣ መኮንን መና (ተከላካይ ከኮንሶ)፣ ሲሳይ ማሞ (ተከላካይ ሶዶ ከተማ)፣ ዘላለም በየነ (የመስመር አጥቂ ከአረካ ከተማ)፣ በኃይሉ በርዛ (ተከላካይ ከተስፋ ጨንቻ ፕሮጀክት)፣ መሠረት ማላቆ (አማካይ ከጨንቻ ተስፋ) ክለቡን የተቀላቀሉ አዲስ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ጋሞ ጨንቻ በክረምቱ ባቱ ላይ ተደርጎ በነበረው የማጠቃለያ ውድድር በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ማደጉ ይታወሳል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ