ሴቶች ዝውውር | ኢትዮ-ኤሌክትሪክ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

አሰልጣኝ መሠረት ማኒን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠረው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ አስር አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

በ2011 በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረውና ባስመዘገው ውጤትም ከአንደኛ ዲቪዚዮን ወርዶ የነበረው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ጥሩነሽ ዲባባ በሁለተኛ ዲቪዚዮን እንደሚሳተፍ በማሳወቁ በምትኩ በነበረበት እንዲቀጥል መወሰኑን ተከትሎ ለሊጉ ዝግጀት እያደረገ ይገኛል፡፡

ለክለቡ የፈረሙት አዲስ ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፡-

ትዕግስት አበራ (ግብ ጠባቂ ከሀዋሳ ከተማ)፣ እታፈራው አድርሴ (ተከላካይ ከአአ ከተማ)፣ አዳነች ጌታቸው (ተከላካይ ከንግድ ባንክ)፣ ቤዛዊት ተስፋዬ (አማካይ ከአአ ከተማ)፣ አዲስ ንጉሴ (አማካይ ከጥረት ኮርፖሬት)፣ ትዕግስት ኃይሌ (አጥቂ ከቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ምንትዋብ ዮሐንስ (አጥቂ ከአአ ከተማ)፣ እማዋይሽ ይመር (አጥቂ ከልደታ ክ/ከተማ)፣ ትመር ጠንክር (ከጥረት ኮርፖሬት አጥቂ)፣ ፍሬወይኒ ገ/ፃዲቅ (አጥቂ ከአአ)

ከአዲሶቹ በተጨማሪ የአጥቂዋ ቤተልሄም ከፍያለው እና የግብ ጠባቂዋ እስራኤል ከተማን ውል ለተጨማሪ ዓመት ያራዘመው ክለቡ አሰልጣኝ መሠረት ማኔ በሴካፋ ሴቶች ዋንጫ ምክንያት ከክለቡ ጋር አብራ ባትኖርም በረዳቶቹ አማካኝነት ለአዲሱ የውድድር ዘመን እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ