እረፍት ላይ የነበረው የማልታ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ትላንት ሲጀመር ትናንት ምሽት ሞስታን በሜዳው ገጥሞ 5ለ1 ሲያሸንፍ ሎዛ አበራ ሦስት ግቦችን አስቆጥራ ሐት-ትሪክ ሰርታለች፡፡
ቢርኪርካራ በሜዳው ቻርለስ አቤላ ስታዲየም አምስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ሞስታን በገጠመበት በዚህ ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ በ37ኛው ደቂቃ ሎዛ አበራ ባስቆጠረችው የመጀመሪያ ግብ 1ለ0 በሆነ ውጤት ወደ እረፍት ያመሩ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ በ75ኛው እና 77ኛው ደቂቃ አከታትላ ባስቆጠረቻቸው ግቦች በማልታ የመጀመሪያ ሐት-ትሪኳን ሰርታለች። ለቢርኪርካራ ቀሪዎቹን ግቦች ደግሞ እንግሊዛዊቷ ኢስተር አኑና ተቀይራ የገባችው ትሬሲ ቴውማ አስቆጥረዋል።
ሎዛ በሊጉ የግብ መጠኗን ወደ 8 በማሳደግ ከሃሌይ ቡጌጃ ጋር በእኩል ጎል የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ሰንጠረዡን መምራት ይዘዋል።
ቢርኪርካራ ከቀናት በፊት የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ ከኮርክ 3ለ3 ሲለያይ ሎዛ በዚህም ጨዋታ ግብ ማስቆጠሯ ይታወሳል፡፡
በሌላኛው የዚህ ሳምንት መርሃግብር ሁለቱ ከቢርኪርካራ ጋር በእኩል ነጥብ ሊጉን ሲመሩ የነበሩት ምጋርና ሴዌኬን ያገናኘው ጨዋታ ሲዊኪ ዩናይትዶች በ13 ነጥብ ከቢርኪርካራ ጋር በመሆን ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛሉ።
© ሶከር ኢትዮጵያ