ኦሮሚያ ዋንጫ ዛሬ ተጀመረ

በአምስት ቡድኖች መካከል በቢሾፍቱ ከተማ የሚካሄደው የኦሮሚያ ከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ ቡድኖች የሚካፈሉበት ውድደር ዛሬ ተጀምሯል።

የኦሮሚያ ዳኞችና ኮሚሽነሮች ማኀበር ከኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ውድድር አምስት ቡድኖች የሚካፈሉ ይሆናል። ገላን ከተማ፣ ቢሾፍቱ ከተማ፣ ባቱ ከተማ፣ ዱከም ከተማ እና ሞጆ ከተማ ተሳታፊ ቡድኖች ናቸው።

የዛሬ ጨዋታ ውጤት

ቢሾፍቱ ከተማ 1–0 ሞጆ ከተማ
ገላን ከተማ 2–1 ዱከም ከተማ

ሰኞ ኀዳር 22 ቀን 2012

08:00 | ገላን ከተማ ከ ባቱ ከተማ

10:00 |
ሞጆ ከተማ ከ ዱከም ከተማ

​


© ሶከር ኢትዮጵያ