ሁለት የባህር ዳር ከተማ ተጨዋቾች የቀድሞ ክለባቸውን ለመክሰስ እንቅስቃሴ ጀምረዋል

በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ወደ ጣናው ሞገዶቹ ያመሩት ሁለት ተጨዋቾች የቀድሞ ክለባቸውን ለመክሰስ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

ባሳለፍነው ዓመት ከጅማ አባጅፋር ጋር ያሳለፉት የተከላካይ መስመር ተጨዋቹ አዳማ ሲሶኮ እና የአጥቂ መስመር ተጨዋቹ ማማዱ ሲዲቤ የቀድሞ ክለባቸው(ጅማ አባጅፋር) የ4 ወር ደሞዝ ስላልከፈላቸው ቅራኔ በማንሳት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ደብዳቤ ማስገባታቸው ይታወቃል። ሁለቱ ተጨዋቾች ሃምሌ 13 እና ነሃሴ 29 2011 ዓ.ም በየግላቸው ደብዳቤ ለፌደሬሽኑ በማስገባት ምላሽ ቢጠባበቁም ከፌደሬሽኑ ምላሽ ሳያገኙ ቀርተዋል።

ተጨዋቾቹ ለመጨረሻ ጊዜ ከህጋዊ ወኪላቸው ጋር በመነጋገር ደብዳቤ ለፌደሬሽኑ ማስገባታቸውን ለሶከር ኢትዮጵያ ያስታወቁ ሲሆን ፌደሬሽኑ በጎ ምላሽ ካልሰጣቸው ግን ክለቡን(ጅማ አባጅፋር) እንዲሁም ፌደሬሽኑን ለፊፋ ለመክሰስ እዳሰቡ ገልፀዋል።

ከተጨዋቾች ደሞዝ ጋር በተያያዘ ዓምና(በተለይ የአመቱ መገባደጃ ላይ) ብዙ ጥያቄዎችን ከተጨዋቾች ሲያስተናግድ የነበረው ጅማ አባጅፋር ከቀናት በፊት ውላቸውን ላራዘሙ እና በቋሚነት ከክለቡ ጋር ለቆዩ ተጨዋቾች የ4ወር ደሞዝ መክፈሉ ተሰምቷል።

ሁለቱ ተጨዋቾች ለየግላቸው ለፌደሬሽኑ ያስገቡት ደብዳቤ የሚከተለው ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ