አዲስ አዳጊው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ የአሰልጣኙ መሐመድ ኑርን ኮንትራት ሲያራዝም አስር አዳዲስ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል።
ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ያስቆጠረው ኮልፌ ቀራንዮ በ2010 ተመስርቶ በ2011 በአንደኛው ሊግ ሲሳተፍ ከቆየ በኋላ ዐምና ባቱ ላይ ተደርጎ በነበረው የማጠቃለያ ውድድር ወደ ከፍተኛ ሊጉ ማደግ ችሏል። ክለቡን ከምስረታው ጀምሮ በአሰልጣኝነት መርተው የነበረው እና በአዲስ አበባ ከተማ ከ17 ዓመት በታች አሰልጣኝ እንዲሁም በፕሪምየር ሊጉ እየተጫወቱ የሚገኙት ሳላዲን በርጌቾ፣ ቶማስ ስምረቱ፣ ምንተስኖት አዳነ እና የመሳሰሉት ተጫዋቾች መሰረት ያስያዙት አሰልጣኝ መሐመድ ኑር ከ2010 ጀምሮ ኮልፌን በአሰልጣኝነት ሲያገለግል የቆየ ሲሆን ለቀጣይ ዓመት በክለቡ እንዲቆይም ውሉ ተራዝሟል።
ቡድኑ ያስፈረማቸው አዳዲስ ተጫዋቾች በግብ ጠባቂ ቦታ ላይ ፖልክ ቾልክ (ከአዲስ ከተማ)፣ በተከላካይ ስፍራ ላይ ጥላሁን ካሣሁን (ከኢትዮጵያ ቡና)፣ አዩብ ዘይኑ (ከየካ ክፍለ ከተማ) እና አበራ (ከልደታ ክፍለ ከተማ)፣ በአማካይ ስፍራ ላይ ያሬድ ዓለማየሁ እና ጥላሁን ከበደ (ከናኑ ሁርቡ)፣ አሸናፊ ካሣ እና አዳነ (ከከፋ ቡና)፣ በአጥቂ ሥፍራ ተመስገን ሙሉጌታ (ከወሎ ኮምበልቻ) እንዲሁም ሀይቀል ደዋሙ (ከቂርቆስ) ናቸው።
© ሶከር ኢትዮጵያ