ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰርቢያ ዜግነት ያላቸውን ጉራን ጉዚያንን በቅርቡ በረዳት እና በአካል ብቃት አሰልጣኝነት መቅጠሩ የሚታወስ ሲሆን አሁን ላይ ግን መለያየታቸው ዕርግጥ ሆኗል፡፡
ከወራት በፊት ቅዱስ ጊዮርጊስን በሁለት ዓመት የውል ኮንትራት በይፋ የተቀላቀሉት እኚህ አሰልጣኝ የረዳት እና የአካል ብቃት አሰልጣኝ ሆነው እንዲሰሩ ተብሎ የመጡ ቢሆንም ክለቡ ከሥራ ፍቃድ ጋር በተገናኘ የመንፈቅ ያህል ቆይታ እንኳ ሳያደርጉ ተለያይዋል። አሰልጣኙ ለመለያየታቸው የሥራ ፈቃድ ጉዳይ ቢነሳም የሙያ አቅማቸው ከተጠበቀው በታች መሆኑ ለስንብታቸው መንስኤ ስለመሆኑም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በአሰልጣኙ ቅጥር ወቅት እግርኳስን ጨምሮ በበርካታ ስፖርቶች ልምድ ማዳበራቸው ቢገለፅም አሰልጣኙ ግን ከውሀ ዋና ጋር ብቻ የተያያዘ ልምድ እንዳካበቱ ሰምተናል።
© ሶከር ኢትዮጵያ