ለ2012 የውድድር ዘመን የስታድየም መግቢያ ዋጋ ማሻሻያ ያደረጉት ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ቡና ይህን አስመልክቶ ደጋፊዎች ለቀረቡት ጥያቄ የክለብ ተወካዮች ምላሽ ሰጥተዋል።
በዘመናዊ አሰራር ራሳቸውን እያደራጁ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ከዓምናው የስታድየም መግቢያ ዋጋ ማሻሻያ በማድረግ የመግቢያ ዋጋ ጭማሪ ማደረጋቸው ይታወሳል። በዚህም መሠረት ክቡር ትሪቩን 300፣ ጥላፎቅ 200፣ ከማን አንሼ ባለ ወንበር 100፣ ከማን አንሼ ወንበር የሌለው 50፣ ካታንጋ 30 እና ሚስማር ተራ፣ ዳፍ ትራክ 20 ብር አዲሶቹ የመግቢያ ዋጋ ተመኖች ናቸው።
በዚህ ዋጋ ጭማሪ ምክንያት የሁለቱም ክለብ ደጋፊዎች በጭማሪው ደስተኛ አለመሆናቸውን በተለያዩ መንገዶች ሀሳባቸውን እየገለፁ ይገኛል። ይህን የቅሬታ ሀሳብ በመያዝ ሶከር ኢትዮጵያ ከክለብ ተወካዮች ጋር አጭር ቆይታ አድርጋለች።
አቶ ሰለሞን የኢትዮጵያ ቡና የደጋፊዎች ማኀበር ም/ፕሬዝደንት ” ጥያቄው በተደጋጋሚ እየመጣልን ይገኛል። ከሚመለከታቸው የክለቡ የበላይ አመራሮች ጋር ቁጭ ብለን ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘናል” ሲሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል እንደሰማነው ከሆነ በሂደት ጥያቄው ሊታይ እንደሚችል እና የስቴዲየም መግቢያ ዋጋ ጭማሪ ሊቀንስ የሚችልበት መንገድ አልያም በዚሁም በአዲሱ ተመን ሊቀጥል እንደሚችል ሰምተናል።
ሁለቱም ክለቦች በቅርቡ ከትኬት ጭያጭ ጋር በተያያዘ በአሞሌ ዳሽን ባንክ ጋር ስምምነት መፈፀማቸው ይታወቃል።
© ሶከር ኢትዮጵያ