የአሰልጣኞች አስተያየት| ወልዋሎ 2-1 ወላይታ ድቻ

በሊጉ ሁለተኛ ሳምንት መቐለ ላይ ወላይታ ድቻን ያስተናገደው ወልዋሎ 2-1 ካሸነፈበት ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች ምክትል አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ቡድኑ በቀጣይ ጊዜ በአጨዋወትም በውጤትም እየተሻሻለ ይሄዳል” አብርሃ ተዓረ – የወልዋሎ ምክትል አሰልጣኝ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው እንዳያችሁት ነው። ቡድኑ ገና በመሰራት ሂደት ውስጥ የሚገኝ ነው። ከጨዋታ ጨዋታ እየተስተካከለ በፈለግነው አጨዋወት እየሄደልን ነው። የሚቀሩን ነገሮች አሉ እነሱን እያስተካከልን ጥሩ ውጤት እናመጣለን ብዬ አስባለው።

ቡድኑ ስለመረጠው አጨዋወት

የመረጥነው አጨዋወት መልሶ ማጥቃት ነው።
ተጋጣሚያችን ኳስ ይዘው ይጫወታሉ ብለን ገምተን ስለገባን ቀድመን በተዘጋጀንበት አጨዋወት አሸንፈን ወጥተናል።

ስለ ቡድኑ ቀጣይ ጉዞ

ቡድኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስተካከለ የሚሄድ ነው። በቀጣይ በአጨዋወትም በውጤትም እየተሻሻለ ይሄዳል።

” ዛሬ ዕድለኛ አልነበርንም ” ደሳለኝ ደቻሳ – የወላይታ ድቻ ምክትል አሰልጣኝ

ስለ ጨዋታው

አቅደን የመጣነው አጥቅተን ለመጫወት ነበር። አጥቅተንም ነው የተጫወትነው፤ ስህተቶች ግን ሰርተናል። እነሱም የኛን ስህተት ተጠቅመዋል። እነሱ በመከላከሉ ረገድ ጥሩ ነበሩ። እኛ ኳሱን ተቆጣጥረን ለመጫወት ሞክረናል። የተቻለን ነገር ሰርተናል ውጤቱ ምንም ይሁን ምን መስራት ያለብን ነገር ሰርተናል ተጫዋቾቻችንም ጥሩ ነበሩ። ዛሬ ዕድለኛ አልነበርንም።

ስለ ሊጉ አጀማመር

ፕሪምየር ሊጉ አጀማመሩ ጥሩ ነው። እዚም ጥሩ አቀባበል ተደርጎልናል በስቴድየም ያለው ነገር ጥሩ ነው። ዘንድሮ በየቦታው ጥሩ ስሜት ነው ያለው፤ ይቀጥል የሚያስብል ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ