ከፍተኛ ሊግ | ሀምበሪቾ ዱራሜ ለፌዴሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤ አስገባ

በከፍተኛ ሊግ እየተሳተፈ የሚገኘው ሀምበሪቾ ዱራሜ ለፌዴሬሽኑ በምድብ ድልድሉ ላይ ያለውን ቅሬታ አሰምቷል።

ባሳለፍነው ረቡዕ በጁፒተር ሆቴል የ2012 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የምድብ ድልድል በ27 ድጋፍ በ9 ተቃውሞ ይፋ መሆኑ ይታወቃል። በዕለቱም ኢኮስኮ፣ ኢትዮጵያ መድን እና ሀምበሪቾ የምድብ ድልድሉ ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደነበር ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ሀምበሪቾ በቀን 27/03/2012 ዕለት ቅሬታ ያዘለ ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ አስገብተዋል ” የምድብ ድልድሉ ፍፁም ኢ-ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የተዘጋጀ ነው። የሥራ አስፈፃሚው በአስቸኳይ ጣልቃ በመግባት ይህን ጉዳይ እልባት እንዲሰጠው እንጠይቃለን። ምድብ ሀ ህግና ደንቡን ጠብቆ የተከናወነ ሲሆን የምድብ ለ እና ሐ ህጉን እና ደንቡን ጠብቆ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ለዳኞች ለኮሚሽነሮች የምንከፍለው ክፍያ አዲሱን ምድብ ታሳቢ በማድረግ አይደለም።” ብለዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ