የኦሮሚያ ዋንጫ በገላን ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል

ለቀናት በቢሾፍቱ ከተማ በአምስት ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ዋንጫ ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ ገላን ከተማ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።

የኦሮሚያ ዳኞችና ኮሚሽነሮች ማኅበር ከኦሮሚያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በተዘጋጀው በዚህ ውድድር አምስት ቡድኖች ተሳትፈዋል። ዛሬ ፍፃሜውን አግኝቶ የተሻለ ነጥብ በመሰብሰብ ገላን ከተማ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኖ አጠናቋል።


ረቡዕ ኀዳር 24 ቀን 2012
ሞጆ ከተማ 0–2 ገላን ከተማ
ቢሾፍቱ ከተማ 1–1 ባቱ ከተማ

ዓርብ ኀዳር 26 ቀን 2012
ዱከም ከተማ 1–0 ቢሾፍቱ ከተማ
ሞጆ ከተማ 3–0 ባቱ ከተማ

እሁድ ኀዳር 28 ቀን 2012
ዱከም ከተማ 1–0 ባቱ ከተማ
ቢሾፍቱ ከተማ 0–0 ገላን ከተማ

በዚህም መሠረት በአጠቃላይ ውጤት በደረጃ
1ኛ ገላን ከተማ – 8
2ኛ ዱከም ከተማ – 7
3ኛ ቢሾፍቱ ከተማ – 4
4ኛ ሞጆ ከተማ – 4
5ኛ ባቱ ከተማ – 2 ነጥቦች በመሰብሰብ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ