ጅማ አባጅፋር ለዘንድሮ የውድድር ዓመት ያስፈረማቸው የሦስቱ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾች ጉዳይ ዕልባት አግኝቷል።
ጅማ አባጅፋርን ዘንድሮ የተቀላቀሉትና የና ዜግነት ያላቸው ግብጠባቂው መሐመድ ሙንታሪ፣ ተከላካዩ አሌክስ አሙዙ እንዲሁም አጥቂው ያኩቡ መሐመድ ከሥራ ፈቃድ ጋር ተያይዞ ያላለቀ ጉዳይ በመኖሩ በመጀመርያው ሳምንት ከባህር ዳር ከተማ ጋር ያለ ጎል በአቻ ውጤት በተጠናቀቀው ጨዋታ ላይ አለመሰለፋቸው ይታወቃል።
ሆኖም በአሁኑ ወቅት የሦስቱም ተጫዋቾች ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በመጠናቀቁ በሁለተኛ ሳምንት የፊታችን ረቡዕ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ እንደሚጫወቱ ተረጋግጧል።
© ሶከር ኢትዮጵያ