ዋልያዎቹ ዳግም ወደ ባህርዳር?

 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ፌዴሬሽኑ ባህርዳር ስታድየም ላይ ለመጫወት ወስኗል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ — የሚደረገው ጨዋታ በባህርዳር እንዲደረግ የወሰነ ሲሆን አሁን የሚቀረው የአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን ፍቃደኝነት ነው፡፡

የአልጄርያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር ያለው መረጃ ጨዋታው አዲስ አበባ እንደሚካሄድ በመሆኑና የኢትዮጵያ ቆይታቸውን በሸራተን ሆቴል ለማድረግ ቀድመው በማስያዛቸው ወደ ባህርዳር ለማስቀየር የማግባባት ስራ እንደሚሰራ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ 3ኛ ጨዋታዎች መጋቢት ወር ላይ ሲደረግ በምድብ 10 የምትኘው ኢትዮጵያ ከ አልጄርያ ጋር በተከታታይ ትጫወታለች፡፡

በ3ኛው ጨዋታ ከመጋቢት 14-16 ባሉት ቀናት አልጀርስ ላይ ስትጫወት በ4ኛው ጨዋታ ደግሞ ከመጋቢት 17-19 ባሉት ቀናት በባህርዳር (ነገሮች በታሰበላቸው መንገድ ከሄዱ) ይጫወታሉ፡፡

ያጋሩ