ሰበታ ከተማ ከሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ

ከዓመታት በኃላ ዳግም ወደ ሊጉ የተመለሰው ሰበታ ከተማ ለአራት ተከታታይ ዓመት የሚቆይ የገንዘብ እና የስፖርት ቁሳቁስ የስፖንሰር ስምምነት ከሜታ አቦ ቢራ ጋር ፈፅሟል።

የክለቡ የበላይ ጠባቂ እና የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሃኑ በቀለ፣ አቶ ኡብሳ ለገሰ የክለቡ ፕሬዝደንት፣ አቶ ከድር ወዳጆ የደጋፊ ማኅበር ፕሬዝደንት፣ ኔታልያ ሴላኒ የሜታ ቢራ የማርኬት ክፍል ኃላፊ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በታደሙበት ነው ማምሻውን በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ስምምነቱ የተፈፀመው።

በስምምነቱ መሠረት ሰበታ ከተማ በማልያው ላይ ምርቱን ያስተዋውቃል። በዚህም በአራት ዓመታት ውስጥ የሚከፈል ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ እና አራት ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁሶችን በማስመጣት ክለቡ ለገበያ አቅርቦ ተጠቃሚ እንዲሆን በድምሩ ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ የስፖንሰር ስምምነት ተፈፅሟል።

ከስፖንሰር ስምምነቱ ጋር ተያይዘው ያሉ መረጃዎችን በቀጣይ በስፋት ይዘን የምንመለስ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ