ከፍተኛ ሊግ | አንጋፋው አጥቂ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል

አንዱዓለም ንጉሴ ወደ ቀድሞ ክለቡ ወልዲያ አምርቷል፡፡

ከሙገር ሲሚንቶ የተገኘውና ለረጅም ዓመታት እየተጫወቱ ከሚገኙ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሰበታ ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ቡና አጥቂ በ2009 እና 2010 በወልዲያ በግሉ ድንቅ ጊዜ ማሳለፍ የቻለ ሲሆን በሁለተኛው ዓመትም ቡድኑን በአምበልነት መምራት ችሎ ነበር።

በ2011 የውድድር ዘመን በወላይታ ድቻ የአንድ ዓመት ቆይታ ካሳለፈ በኋላ ቀድሞ ይጫወትበት ወደነበረው እና በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ሊግ ለሚገኘው ወልዲያ ዳግም ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ