የአሰልጣኞች አስተያየት | ሰበታ ከተማ 0-0 አዳማ ከተማ

በ3ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሰበታ ከተማና አዳማ ከተማ ያለግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም የሁለቱ ክለቦች አሰልጣኞች ቡድን አባላት ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

“ከዕለት ወደ ዕለት የራስ መተማመናችን እያደገ ሲመጣ ነገሮች ጥሩ እየሆኑ ይመጣል” ውበቱ አባተ – ሰበታ ከተማ

ስለ ጨዋታው

“ከተከታታይ ሽንፈቶች በኋላ ያደረገነው እንደመሆኑ ጨዋታው ከባድ ነበር። ተከታታይ ሽንፈት ይዞት ከሚመጣው ሽንፈት ለመውጣት ልጆቼ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። የገጠምነው ቡድን ለዓመታት አብሮ የተዋሃደ ቡድን እንደመሆኑና ከነበረው የደጋፊ ቁጥር ማነስ አንፃር ለእነሱ ጨዋታው ከሜዳ ውጭ ነው ለማለት ይከብዳል። እንደ ቡድን መሻሻሎችን አሳይተናል። በቀጣይ ከዕለት ወደ ዕለት የራስ መተማመናችን እያደገ ሲመጣ ነገሮች ጥሩ እየሆኑ ይመጣል።”

“ጨዋታው በታክቲክ የታጠረ ነበር” አስቻለው ኃይለሚካኤል – አዳማ ከተማ (ምክትል አሰልጣኝ)

ስለ ጨዋታው

“በሁለቱም ቡድኖች በኩል ተመጣጣኝ የጨዋታ እንቅስቃሴ ነበር። ጨዋታው ሁለቱም ተፎካካሪ የሆኑ ቡድኖች መካከል እንደመደረጉ ጨዋታው በታክቲክ የታጠረ ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ ይበልጥ አጥቅተን ተጫውተናል፤ በዚሁ ወቅትም የፈጠርናቸውን አጋጣሚዎች ያለመጠቀም ነገር ነው እንጂ የተሻለ አጥቅተን ለመጫወት ሞክረናል።”


© ሶከር ኢትዮጵያ