የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ ሴካፋን በምክትል ፕሬዝዳንትነት ለመምራት ከሌሎች ተፎካካሪዎች ጋር ለምርጫ ይወዳደራሉ፡፡
የሴካፋ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ የፊታችን ረቡዕ በዩጋንዳ መዲና ካምፓላ ይደረጋል፡፡ በጉባዔው ላይ በሴካፋ ውድድሮች በታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ከመወያየት ባለፈ በተጓደሉ አባላት ምትክ ምርጫ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ከነዚህ መካከል ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ሴካፋን በምክትል ፕሬዝዳንትነት ለመምራት በሚደረገው ምርጫ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ጅራ ቦታውን ለመያዝ በምርጫው እንደሚካፈሉ ታውቋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ለምርጫው በቂ ዝግጅት ሲያደርጉ እንደነበር የገለፁ ሲሆን በምርጫው የሚሳካላቸው ከሆነም ለኢትዮጵያ አንድ እድገት መሆኑን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ