ቻን 2016፡ ዴ. ሪ. ኮንጎ ለሁለተኛ ግዜ የቻን ሻምፒዮን ሁናለች

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ማሊን 3-0 በማሸነፍ የአፍሪካ ሃገራት ዋንጫን ለሁለተኛ ግዜ ማሸነፍ ችላለች፡፡ ለፍሎረንት ኢቤንጌ ቡድን የማሸነፊያ ግቦቹን ሚቻክ ኤሊያ እና ጆናታን ቦሊንጊ አስቆጥረዋል፡፡ ኤሊያ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ለኮንጎ አሸናፊነት ቁልፍ ሚና ተወጥቷል፡፡ ውጤቱ ኮንጎን የቻን ዋንጫን ለሁለተኛ ግዜ ያሸነፈች ብቸኛዋ ሃገር ሲያደርጋት ምዕራብ አፍሪካ ሃገራት ዋንጫው ለመጀመሪያ ግዜ
የማንሳት ፍላጎታቸው መና ቀርቷል፡፡ የኮንጎ ብሄራዊ ቡድን አባላት ከጨዋታው አስቀድመው የደስታ ድግስ ማዘጋጀታቸው አስገራሚ ሁኗል፡፡

በጊኒ እና ኮትዲቯር መካከል ለሶስተኛ ደረጃነት በተደረገው ጨዋታ ዝሆኖቹ 2-1 በማሸነፍ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሁነዋል፡፡ የድል ግቦቹን የጊኒው መሃመድ ዮላ (በራሱ ግብ ላይ) እና ጋባግነን ባዲ በመጀመሪው አጋማሽ ከመረብ አዋህደዋል፡፡ በጨዋታው ሁለት ፍፁም ቅጣት ምት ያመከነው የዝሆኖቹ ግብ ጠባቂ አብዱልከሪም ሲሴ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጧል፡፡ ጊኒን ከመሸነፍ ያላዳነች ግብ አቡበከር ሊዮ ካማራ በስሙ አስመዝግቧል፡፡

ያጋሩ