የ14ኛው የአአ ከተማ ዋንጫ የኮከቦች ምርጫ በቀጣይ ሳምንት ይካሄዳል

በደማቅ ሁኔታ ባሳለፍነው ወር የተጠናቀቀው የ14ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የመዝጊያ ሥነ ስርዓት በቀጣይ ሳምንት በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል ይካሄዳል።

ከጥቅምት 29 – ኅዳር 14 ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 14ኛው የአአ ከተማ ዋንጫ የማጠቃል

ለያ መርሐግብር ማክሰኞ ታኀሳስ 14 ቀን ከቀኑ 08:00 በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል በልዮ ሁኔታ ይካሄዳል። በዕለቱ የሚካሄዱ ዋና ዋና ኩነቶች፡-

– የውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝ ፣ ተጫዋች፣ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ እና የውድድሩ ምርጥ ጎል ሽልማት ይካሄዳል።

– ለአዲስ አበባ እግርኳስ እድገት ከፍተኛ አስተዋፆኦ ላበረከቱ ግለሰቦች የክብር የዕውቅና ሽልማት ይሰጣል።

– በውድድሩ ላይ ከአንድ እስከ ስምንት ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁ ክለቦች ከወጪ ቀሪ የገንዘብ ሽልማት ይበረከታል።

የዘንድሮው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በሁሉም ቀናት 173,484 ተመልካች ታድመውበት ውድድሩ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቻምፒዮንነት መጠናቀቁ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ