የአዳማ ተጫዋቾች ወደ ልምምድ ተመለሱ

ያለፉትን ሁለት ቀናት ከደመወዝ ክፍያ ጋር በተገናኘ ልምምድ አቁመው የነበሩት የአዳማ ተጫዋቾች ዳግም ተመልሰዋል፡፡

ከሁለት ቀናት በፊት የአዳማ ከተማ ነባር ተጫዋቾች ከሁለት ወራት የደመወዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ እንዲሁም አዲስ ክለቡን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ደግሞ የተገባልን ጥቅማጥቅም በአግባቡ አልተፈፀመልንም በማለት በተደጋጋሚ ሲጠይቁት የነበረው የይከፈለን ጥያቄ ባለመመለሱ ልምምድ ሊያቆሙ መገደዳቸውን እና እንዳቆሙም ጭምር በድረገፃችን መግለፃችን ይታወሳል፡፡

አሁን ላይ የክለቡ የበላይ አካላት በወሰዱት አፋጣኝ ምላሽ እና በቅርቡ ተፈፃሚ እናደርጋለን በማለታቸው ተጫዋቾቹ ወደ መደበኛ ልምምዳቸው የተመለሱ ሲሆን በቀጣዩ ቅዳሜ አዳማ በሜዳው ወላይታ ድቻን በአራተኛው ሳምንት ለመግጠም ጠንካራ ዝግጅት ማድረግም ጀምረዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ