ከፍተኛ ሊግ አጫጭር | ልደቱ ለማ ስለ ሐት-ትሪኩ እና ወቅታዊ አቋሙ ይናገራል

እሁድ ከተካሄዱ የከፍተኛ ሊጉ ጨዋታዎች መካከል ለገጣፎ ለገዳዲ በሜዳው ደሴ ከተማን አስተናግዶ 4-3 ማሸነፉ ይታወሳል። በጨዋታው ድንቅ እንቅስቃሴ ያደረገው ልደቱ ለማ ሐት-ትሪክ መስራት ችሏል። ከሶከር ኢትዮጵያ ቆይታ ያደረገው ልደቱ ስለ ሀትሪኩ ይናገራል።

የእግርኳስ ህይወቱን በሙገር ቢ ቡድን ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለው ልደቱ ስሑል ሽረ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድግ ጉልህ አስተዋጽኦ ሽረ በ2011 ለግማሽ ዓመት በባህር ዳር ተጫውቷል።

ስለ ሐት-ትሪኩ

በጣም ነው ደስ ያለኝ። የመጀመሪያ ጨዋታችን በሜዳችን አድርገን ሦስት ነጥብ ማሳካት ችለናል፤ ጨዋታውም ጠንካራ ነበር። ተጋጣሚያችን ጠንካራ ነው። ውጤቱን ለየት የሚደርገው በጉዱሉ ተጫዋች እየተጫወትን ማሸነፋችን ነው። በሜዳችንም የተሻለ ጨዋታ አሳይተን ወጥናል። ሦስት ጎልም በማስቆጠሬ እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ።

ከእረፍት መልስ ብዙ ጎል ስለማስቆጠራችሁ

የመጀመሪያው አጋማሽ ጎል ካስቆጠርን በኋላ ዕድሎች አግኝተን ሳንጠቀምበት ቀርተን ነበር። ከእረፍት መልስ ስንመለስ ነው በሦስት ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ተጫዋች በሁለት ቢጫ የወጣብን ጎል አግብተን መውጣት እንዳለብን አሰልጣኛችን ነግሮን ነበር ያንን ለመፈፀም ያለንን ሁሉ አሟጠን ነው የተጠቀምነው በጉዱሉ ስትጫወት የዛን ቦታ ለመሸፈን ሁሉም አስተዋፅኦ አድርጉል ሜዳው ውስጥ የነበረው ዳኝነት እንዲሁም ከውጭ የነበረው ተፅዕኖ እኛን የበለጠ አብርትቶናል። የተሻለም ግብ አስቆጥን እንድንወጣ እረድቶናል።

ከቡድኑ እና ከልደቱ ምን እንጠብቅ

በጣም አሪፍ አጀማመር ነው የጀመርነው፤ ለዋንጫ እንጫወታለን ። በኔ በኩል ያለውን ፈጣሪ ያውቃል የተቻለኝን ሁሉ ለቡድኑ የሚጠቅመውን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ።

ከፋሲል አስማማው ጋር ስላለው ጥምረት

በጣም አሪፍ ነው! ብዙ እንግባባለን በጣም ጓደኛዬም ነው። ሜዳ ላይም ትሬይኒንግ ላይም ጥሩ ተግባብተን እንሰራለን፤ እንጫወታለን። ቡድኑ ባሁኑ ሰዓት ያለው መነቃቃት እና የቡድኑ መንፈስ እጅግ በጣም ደስ ይላል።

መርሐ ግብር

የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች እሁድ ታህሳስ 12 በ9:00 ላይ የሚደረጉ ይሆናል።

ምድብ ሀ

ደሴ ከተማ 9:00 አቃቂ ቃሊቲ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ 9:00 ወሎ ኮምበልቻ
ፌዴራል ፖሊስ 9:00 ደደቢት
ሶሎዳ ዓድዋ 9:00 ወልድያ
ሰ/ሸ/ደብረ ብርሃን 9:00 ገላን ከተማ
ለገጣፎ ለገዳዲ 9:00 አክሱም ከተማ

ምድብ ለ

መከላከያ 9:00 ነቀምቴ ከተማ
ሀምበሪቾ 9:00 ጅማ አባቡና
ሀላባ ከተማ 9:00 ኢኮስኮ
ጋሞ ጨንቻ 9:00 አዲስ አበባ ከተማ
ቤንች ማጂ ቡና 9:00 ሻሸመኔ ከተማ

ምድብ ሐ

ኢትዮጵያ መድን 9:00 ስልጤ ወራቤ
ጌዲኦ ዲላ 9:00 ከንባታ ሺንሺቾ
ደቡብ ፖሊስ 9:00 አርሲ ነገሌ
አርባምንጭ ከተማ 9:00 የካ ክ/ከተማ
ባቱ ከተማ 9:00 ቡታጅራ ከተማ
ኮልፌ ቀራኒዮ 9:00 ቂርቆስ ክ/ከተማ


© ሶከር ኢትዮጵያ