ዲሲፕሊን ኮሚቴው አሰልጣኝ ሥዩም ከበደን ለማናገር ቀጠሮ ያዘ

በአዲስ መልክ የተዋቀረው የኢትዮጵያ እግርኳስ ዲሲፕሊን ኮሚቴ አሰልጣኝ ሥዩም ከበደን በቀጣይ ሳምንት ለማናገር ቀጠሮ ይዟል።

በሦስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሆሳዕናው አቢዮ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም ወልቂጤ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ ያደረጉት ጨዋታ በወልቂጤ ከተማ 1-0 በሆነ አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል። አሰልጣኝ ሥዩም ከበደም ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በተለይ በግል ፌስቡክ ገፃቸው ላይ የሆሳዕናው አቢዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ለጨዋታ ምቹ እንዳልነበረ ዘርዘር ያለ የግል አስተያየታቸውን መፃፋቸው ይታወቃል።

የዲሲፕሊን ኮሚቴው ይህን ተከትሎ ይመስላል ሰኞ ታኀሳስ 20 ቀን ከቀኑ 09:00 ላይ በአዲስ አበባ ስታድየም ቢሮ በፁሑፉ ዙርያ ማብራሪያ እንዲሰጡ አሰልጣኙን ለማናገር ቀጠሮ ይዟል።

አሰልጣኝ ሥዩም በፌስቡክ ገፃቸው ያሰፈሩት ፅሁፍ ይህን ይመስላል፡-


© ሶከር ኢትዮጵያ