ኳታር 2022 | ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ድልድል የሚገኙበት ቋት ተለየ

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን በመጪው ጥር በግብፅ ካይሮ ከሚካሄደው የ2022 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ድልድል አስቀድሞ አራት ቋቶችን ይፋ አድርጓል። ዋሊያዎቹም በ4ኛው ቋት ላይ ተመድበዋል።

በ10 ምድቦች ተከፍሎ የሚካሄደው የአፍሪካ ዞን ማጣርያ 40 ሀገራትን የሚያሳትፍ ሲሆን ወቅታዊ የዐለም ሀገራት ደረጃን መሠረት በማድረግ ቡድኖቹን በአራት ቋት መድቧል። 146ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙት መካከል የሚገኝ በመሆኑ የመጨረሻው ቋት ላይ ተደልድሏል። በዚህም በቋት አንድ፣ ሁለት እና ሦስት ከሚገኙና ደረጃቸው ከፍ ካሉ ሀገራት ጋር በአንድ ምድብ ሊደለደል ይችላል።

ኢትዮጵያ ከሌሶቶ ጋር በድምር ውጤት 1-1 ተለያይቶ ከሜዳ ውጪ ባስቆጠረው ጎል አማካኝነት ወደ ምድብ ዙር ማለፏ የሚታወስ ነው።

በመጋቢት ወር በሚጀመረው የምድብ ጨዋታ በየምድቡ አንደኛ ደረጃ ይዘው የሚጨርሱ አስር ሀገራት በመለያ ጨዋታ እርስ በርስ ተጫውተው አሸናፊ የሚሆኑ 5 ሀገራት የኳታር ትኬታቸውን ይቆርጣሉ።

የቋት ዝርዝር

አንድ፡ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ናይጄርያ፣ ፣ አልጄርያ፣ ሞሮኮ፣ ጋና፣ ግብፅ፣ ካሜሩን፣ ኮንጎ ዲሪ.፣ ማሊ

ሁለት፡ ቡርኪና ፋሶ፣ አይቮሪኮስት፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጊኒ፣ ዩጋንዳ፣ ኬፕ ቨርድ፣ ጋቦን፣ ቤኒን፣ ዛምቢያ፣ ኮንጎ

ሦስት፡ ማዳጋስካር፣ ሞሪታንያ፣ ሊቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ኬንያ፣ መካ. አፍሪካ ሪፐ.፣ የዚምባብዌ፣ ኒጀር፣ ናሚቢያ፣ ጊኒ ቢሳው

አራት፡ ማላዊ፣ አንጎላ፣ ቶጎ፣ ሱዳን፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ፣ ኢኳ. ጊኒ፣ ኢትዮጵያ፣ ላይቤርያ፣ ጅቡቲ


© ሶከር ኢትዮጵያ