በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 4ኛ ሳምንት በካሣዬ አራጌ የሚመራው ኢትዮጵያ ቡና ሀዋሳ ከተማን ከሙሉ የጨዋታ ብልጫ ጋር 4-1 ካሸነፈበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።
“ተጋጣሚያችን በገመትነው መልኩ ነበር የቀረበው” ካሳዬ አራጌ – ኢትዮጵያ ቡና
” ከእረፍት በፊት ተጋጣሚያችን በገመትነው መልኩ ነበር የቀረበው። ይህም በፈልገነው መልኩ እንድንቀሳቀስ ረድቶናል። በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታው በገመትነው መልኩ ነው የሄደው። ምክንያቱም እየተመሩ ስለነበር ምንም በራሳቸው ሜዳ ሊቀሩበት የሚችሉበት ምክንያት ባለመኖሩ ነቅለው ወደ እኛ ሜዳ እንደሚመጡ አስበን ነበር፤ በዛ ረገድ ነቅለው የመጡበት ነበር። ነገርግን እኛ ባቀድነው ልክ እነሱን ተቆጣጥረን መጫወት ሙሉ ለሙሉ አልቻልንም፤ ስለዚህ ለቀጣይ ጨዋታዎች በርካታ ቀሪ ነገሮች እንዳሉ አሳይቶናል።
“ከወትሮው በተለዩ መዘናጋቶች ነበሩብን” አዲሴ ካሣ – ሀዋሳ ከተማ
ስለጨዋታው
“ጨዋታው ያልጠበቅነው ነው፤ በመጀመሪያው አጋማሽ ከወትሮው በተለየ መዘናጋቶች ነበሩ።ኢትዮጵያ ቡናዎች ከኳስ ውጭ ያላቸው እንቅስቃሴ ጥሩ ነበር ይህም ለእኛ ተጫዋቾች ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሆኖባቸው ነበር። በተለይ በመጀመሪያ አጋማሽ የነበሩ ክፍተቶችን በሙሉ እየተጠቀሙብን ነበር፤ በአጨራረስ ረገድም የተሻሉ ነበሩ። በዚህም ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ችለዋል።”
ስለ ግብ ጠባቂያቸው
” በእግርኳስ ስህተቶች ይከሰታሉ። የውጭ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የእኛ ሀገር በረኞች መሰል ስህተቶች ሊሰሩ ይችላሉ።”
© ሶከር ኢትዮጵያ